እውነት የጠማው ሰው (THE MAN THIRSTY OF TRUTH)


 “እውነት እና ውሃ ምንጊዜም ከላይ ነው።” (ልምድ (የተለመደ) ጥቅስ)

“ሀሰት ስለበዛ፣ እውነት ሆነ ዋዛ” (ዳንኤል አበራ፣ የአማርኛ ተረትና ለምሣሌዎች፣ ፲፱፻፺፰፣ ባለሶስት ትእይንት በመደበኛ እና ሰውኛ ዘይቤ ተቀላቅሎ የተፃፈ። ገ.፫፤ አሃዛዊ ቅጂውን ያግኙ


በዳዊት ደገፉ (ሐረር እርሻ ኮሌጅ)፣ ህትመት ተስፋ ማተሚያ ፲፱፻፵፱፣ ባለሶስት ትእይንት በመደበኛ እና ሰውኛ ዘይቤ ተቀላቅሎ የተፃፈ አስቂኝ፤ በረቂቅ ጉዳዮች የሚመራር፤ ልብወለድ ድራማ፨

 • ትልም


እውነት በውሸት፥ ምቀኝነት፥ ክፋት፥ ጭካኔ፥ ቅሌት፥ ተንኮል፥ ስንፍና፥ እና አባታቸው ሠይጣን ተጠልቶ እንዲወገድ በማህበራቸው ተወስኖበት ሊሰቅሉት ሲል፣ መልኣክ ከእግዚአብሄር ተልኮ ያድነዋል፤ ቃራኒዎቹ ይገደላሉ፤ እየወደቀ ሳለ እንደምንም ያልተለዩት ፍቅር፥ ተስፋ፣ ክብር እና እምነትም ተጨምረው በሰው ህይወት ዳግመኛ እንዲያንሰራሩ ይወስናሉ፨

ይህም፧

በትእይንት ፩ኛ፧ እውነት መሀላሀሰት አይቶ፣ መተማመንም ተከድቶ፣ በብስጭት ለሁለት ሆነው ከውሸት ጋር ሃሳባዊ ጥል ያረጋሉ። እውነት ማመንን የውሸትን እና የመከዳዳትን ነገረስራ፣ መሸነፋቸው የማይቀር መሆኑን እያስረዳ እስከ ምጽኣት እንዲበረታ ይመክረዋል። ደስተኛ ምቀኝነትም አጊንቷቸው ያገኛቸውን ታታሪዎች ጠልቶ ስንፍናን ጠርቶ በመላክ አስንፎ እንዳሰናከላቸው ያሳውቃቸዋል። በተፈጠረ ሙግትም ምቀኝነት እውነትን ለመግደል ማቀዱን አሳውቆ በመዛት ይሄዳል። ማመን ተቃራኒዎቹን ሲፈራ እውነት አደፋፍሮት እንዲመርጥ ይጠይቀዋል፤ የማታማታ የእውነትን አይሸነፌነትን ተነጋግረውበት በመቀበል አብሮነታቸውን ያድሳሉ።

በትእይንት ፪ኛ፧ ቅሌት እና ክብር ተጣልተው እውነት እና አመነ ጋር ሄደው ተካሰሱ። ቅሌት ሰው አስክሮ ከሌላ በማጣላቱ ክብር ተበሳጭቶ ተለየ። ቅሌት በስካር አስደሳችነት ተመስጦ ባለመስማማት ሲሄድ፣ ተስፋ ይመጣና በመቆጨት ፋንታ ለመበርታት እና ለመጠንከር እንዲረዳው የእውነትን እግዝ ይጠይቃል። በእግዜር መመካትን አጠንክረው ለሚያቃቸው የሰው እጅ ሁሉ ይወስንበት ብለው ይተዋሉ፨

በትእይንት ፫ኛ፧ በሐሰት ቤት ተገኝተው፣ ሐሰት፥ ቅሌት፥ ተንኮል፥ ምቀኝነት፥ ስንፍና፥ ክፋት እና ጭካኔ፣ ከንትርክ-ዱለታ በኋላ በአባታቸው ዲያቢሎስ ፊት ከሰውት ሐሰት ለክፋት ጠብቆ (ጥብቅና ቆሞ)፣ በእውነት ላይ ስቅላት ያስፈርዳሉ። ጭካኔ ፈፃሜ-ፍርድ ሆኖ እውነትን ሰቅሎ የእግር-ስር ጠረጴዛውን ሲያነሳ መልአክ ገመዱን በጠሰ። እግዚአብሔር መፍረዱን፣ በእውነት ፅናት መላእክትም መደሰታቸውን አብስሮ፣ አበርትቷቸው፣ በግራው አብሮት ለመጣው ሞት እነ ክፋትን ረግሞ ሰጠ፤ እሱም ሰበሰባቸው። ፅናትን አሳስቧቸው መልአኩ ሲሰወር፣ እውነት፥ ፍቅር፥ ማመን እና ተስፋ ፅናታቸው መክፈሉ አርክቷቸው በየሰው ልብ ሊሰርጉ ያቅዳሉ። ባንድነትም፤ ሀሠት ስለማታርስ እውነት የጠማው ሰው ጉዳዪን ሁሉ እንዲያጤን ይመክራሉ፨

 ጭብጥ


የመጽሐፉ ፍሬነገር በእውነት ስለመፅናት ነው። ሐሰት ለወደፊት ቅጣትን ያመጣል፤ አምላክም ይገስፀዋል፤ እውነትም ከክብር ጋርም ሆነ ከፍቅርና ማመን ጋር አይለያዩም፨

በተጨማሪም፤ ሐሰተኛነት በራሱ ከመጉዳቱ ቀጥሎ ለመቆየት ሲል ጭካኔን፣ ምቅኝነትን፣ ተንኮል፣ ስንፍናን ወዘተ...ን ያጎለብታል። ያዳቆነ እንዲሉ ሌላም ደግሞ ጉዳቱ ወደሰይጣን ያደርሳል፥ አስቀድሞም ገንዘብነቱ (እሚገዛበት’፥ የእምለው ከገባችሁ) የእርሱ ነውና። አንድም ሲከፋ ወይንም አንድም መቋጫው ላይ ክፉ፣ ሞት ሊያመጣ ይችላል ሁሉ፨

 ጥቅሶች


 • ሰው ፈፅሞ እንዳይወድቅ ተስፋ በሚባል ምርኩዙ ይደገፋል። (መግቢያ)

• አንድቀን በድንገት ችግር ቤቴ ገብቶ፤
ወዳጆቼን ሁሉ አሳየኝ አጉልቶ። (ገ. ፯)

• የሰው ልጅ ሳቅ ሲል ጥርሶቹ በሙሉ፤
ነጭ እንደበረዶ ወተት ይመስላሉ፤
ልቡን ብትመረም ወረድ ብለህ፤
በጨለማ ባህር ትነከራለህ። (ገ. ፱)

 • በድብቅም ሆነ አለዚያም በይፋ፤
ወዳጅን መክዳት ነው ገንዘቡ ሲጠፋ። (ገ. ፱)

  • ብቻ የሚገርመኝ በጣም የሚደንቀኝ፤
አንዳንድ የተማረ አጥፊ ሆኖ ሲገኝ፤
እንደዚህ ያለውን ዐዋቂው ሲሠራ፤
እምባዬም ከመዝነም ምንም አያባራ፤
ጽሕፈት ማወቅና ሂሳብ ተጨምረው፤
ዕውቀቶች በመላ ባንድነት ተባብረው፤
ለምን የሰውን ልጅ አይገሩም ጠንክው፤
በሕፃንነቱስ የሰው ልጅ መማሩ፤
ሊለይ አይደለም ወይ ጉድፉን ከጥሩ'፨ (ገ. ፲፪)

 • እንግዲህ ያሰብኩት አንዴ ከተሰራ፤
ሞትንም ባገኘው በፍፁም አልፈራ። (ገ. ፲፭)

 • የመከራ ካፊያ ያበሰበሰው፤
ትግስትን ሲለብሳት ይሞቃል ገላው። (ገ. ፲፱) 

• ጠጥቶ ሲሰክር ከሚደፍር ሰው፤
ምንም ቢንሰፈሰፍ ይሻላል ፈሪው። (ገ. ፳፫)

 • አንድም ሐሰት ጠፍቶ እውነት ካልደረጀ፤
ክብርም ሊጎለምስ ቅሌት ካላረጀ፤
የዚህ አለም ኑሮ በፍፁም አልበጀ፤
እውነት ተሸፍኖ በውሸት መጋረጃ፤
እንዴት ይዘለቃል እረ እንጃ እንጃ። (ገ. ፳፭ - ፳፮)

 • ሐሰት ክደት ክፋት ደግሞም መመቅኘት፤
ስንፍናና ተንኮል በዚያም ላይ ቅሌት፤
ጭካኔና ስካር ያንደበት ግድፈት፤
የልብም መታወር ሰውን እንዲያረክሱት፤
በአእምሯችሁ ያዙ እንግዲህ አትርሱ፤
እውነትና ፍቅርን ወዳጆች አድርጉ፤ በስጋም በነፍስም እንድትበለፅጉ። (ገ. ፴፫)

• ሐሰትን ቢጠጣት ስለማታርሰው፤
ቢያውቅበት ይሻላል እውነት የጠማው ሰው። (ገ.፴፬)

                     ----ሐ----

ቢንያም ኃይለመስቀል፤ ፪፻፻፲፪ 

Comments

Popular posts from this blog

SOME POPULAR ETHIOPIAN SAYINGS AND PROVERBS WITH THEIR TRANSLATION AND EXPLANATION IN ENGLISH. 2

SOME POPULAR ETHIOPIAN SAYINGS AND PROVERBS WITH THEIR TRANSLATION AND EXPLANATION IN ENGLISH.1

SOME POPULAR ETHIOPIAN SAYINGS AND PROVERBS WITH THEIR TRANSLATION AND EXPLANATION IN ENGLISH. 8