ገበሬውና ሚስቱ (THE FARMER AND HIS WIFE በተፈሪ ደፈረሱ (ዘደብረ ሊባኖስ) የተደረሰ፣ እትም ፲፱፻፵፱፣ የተረዳ (ኢለስትሬትድ) ግጥመ-ልብወለድ ነው። • ትልም ሁለት ጥንድ ገበሬዎች በድህነት፤ ግን በአክብሮት፤ ሲኖሩ የሚስት ጥብቅ መካሪነት፣ አስተዋይነት፣ እና ብሩህነገን ናፋቂነት የተሻለውን ጊዜ ፈጥሮ አስደሳች እና ስኩ ቤተሰባዊ ህይወቶች ሲመጡ ያሳያል። የድሀድሀ ገበሬ በረሀብ የሚስቱን ትእግስት ይፈትናል። ሚስት ነገርግን ታጋሸነትን በመስበክ ባሏን ጥቅመ ቁጠባን አጣፍጣ ታስተምራለች። እንደተለመደው በእየለቱ ያለውን ምግብ በመመገብ ለነገ ባዶ ከመሆን ይልቅ፣ ከተለመደው ውጭ ምግቡን እያሻገሩ ተርበው በመቆጠብ እንዲኖሩ ታደርጋለች። መራራ ህይወታቸውን ለመቀየር ሚስት ባሏን በማነሳሳት፣ በቀለብነት ያጎደለችውን ዘር በልመና ከቤቶቿ (የቀድሞ ቤተሰብ) ተበድራ በማግኘት ሐምሌን እንዲያርስ ታደርጋለች። እስከ ጥቅምት ድረስ በጥን ችግር፤ ግን በስረ ማሳው እንደጠነከሩ፤ ጥቅምት ውስጥ በትኩስ እሸቶች ይንበሸበሻሉ። ከብቶቻቸውም አርሰዋልና-ሰብል-እስኪደርስልን-ይሸጡ-ከሚለው ቅድመ-መኸር የአስገዳጅ-መፍትሔነት በሚስት ቁጡ ውሳኔ ተረፉ፨ በህዳር፤ ለድግሱ የእህል ግብአቶችን ተበድረው፣ ደቦ ይጠራሉ። የስረ ማሳቸው ስኬት ዜና ተሰምቶ የበቀለው ታጭዶ ባል በሚትስ ፈቃድ የስራእድል የለመነውን አጋዥ እንዲሆነው ይቀጥራል፤ ለሷም ደንገጡር አርጉኝ ያለችን ይቀጥራሉ። ህይወታቸው በኑሯቸው ተሻሽሎ፣ እዳዎቻቸው ተመልሰው፣ በማህበረሰቡ ተከብረው፣ የካቲት ላይ በደስታ ግብር ከፍለው፣ ወደሚስት ቤቶች ብዙ ስጦታ አስይዘው ከቀጠሯቸው ጋር ለፋሲካ አክፋይ፣ በዚህኛው ጊዜ ብልፅግ አስችሏቸው፣ ይሄዳሉ። ደስተኛ ጊዜ አሳልፈው “ሰው መሆናቸውን” ካሳዩ ወዲያ፣...
Posts
Showing posts with the label summary of an Amharic poem-novel