Posts

Showing posts from February, 2020
እውነት የጠማው ሰው (THE MAN THIRSTY OF TRUTH)  “እውነት እና ውሃ ምንጊዜም ከላይ ነው።” (ልምድ (የተለመደ) ጥቅስ) “ሀሰት ስለበዛ፣ እውነት ሆነ ዋዛ” (ዳንኤል አበራ፣ የአማርኛ ተረትና ለምሣሌዎች፣ ፲፱፻፺፰፣ ባለሶስት ትእይንት በመደበኛ እና ሰውኛ ዘይቤ ተቀላቅሎ የተፃፈ። ገ.፫፤ አሃዛዊ ቅጂውን ያግኙ ፧ በዳዊት ደገፉ (ሐረር እርሻ ኮሌጅ)፣ ህትመት ተስፋ ማተሚያ ፲፱፻፵፱፣ ባለሶስት ትእይንት በመደበኛ እና ሰውኛ ዘይቤ ተቀላቅሎ የተፃፈ አስቂኝ፤ በረቂቅ ጉዳዮች የሚመራር፤ ልብወለድ ድራማ፨  • ትልም እውነት በውሸት፥ ምቀኝነት፥ ክፋት፥ ጭካኔ፥ ቅሌት፥ ተንኮል፥ ስንፍና፥ እና አባታቸው ሠይጣን ተጠልቶ እንዲወገድ በማህበራቸው ተወስኖበት ሊሰቅሉት ሲል፣ መልኣክ ከእግዚአብሄር ተልኮ ያድነዋል፤ ቃራኒዎቹ ይገደላሉ፤ እየወደቀ ሳለ እንደምንም ያልተለዩት ፍቅር፥ ተስፋ፣ ክብር እና እምነትም ተጨምረው በሰው ህይወት ዳግመኛ እንዲያንሰራሩ ይወስናሉ፨ ይህም፧ በትእይንት ፩ኛ፧ እውነት መሀላሀሰት አይቶ፣ መተማመንም ተከድቶ፣ በብስጭት ለሁለት ሆነው ከውሸት ጋር ሃሳባዊ ጥል ያረጋሉ። እውነት ማመንን የውሸትን እና የመከዳዳትን ነገረስራ፣ መሸነፋቸው የማይቀር መሆኑን እያስረዳ እስከ ምጽኣት እንዲበረታ ይመክረዋል። ደስተኛ ምቀኝነትም አጊንቷቸው ያገኛቸውን ታታሪዎች ጠልቶ ስንፍናን ጠርቶ በመላክ አስንፎ እንዳሰናከላቸው ያሳውቃቸዋል። በተፈጠረ ሙግትም ምቀኝነት እውነትን ለመግደል ማቀዱን አሳውቆ በመዛት ይሄዳል። ማመን ተቃራኒዎቹን ሲፈራ እውነት አደፋፍሮት እንዲመርጥ ይጠይቀዋል፤ የማታማታ የእውነትን አይሸነፌነትን ተነጋግረውበት በመቀበል አብሮነታቸውን ያድሳሉ። በትእይንት ፪ኛ፧ ቅሌት እና ክብር ተጣልተው እውነት እና አመነ ጋር
ገበሬውና ሚስቱ (THE FARMER AND HIS WIFE በተፈሪ ደፈረሱ (ዘደብረ ሊባኖስ) የተደረሰ፣ እትም ፲፱፻፵፱፣ የተረዳ (ኢለስትሬትድ) ግጥመ-ልብወለድ ነው።  • ትልም ሁለት ጥንድ ገበሬዎች በድህነት፤ ግን በአክብሮት፤ ሲኖሩ የሚስት ጥብቅ መካሪነት፣ አስተዋይነት፣ እና ብሩህነገን ናፋቂነት የተሻለውን ጊዜ ፈጥሮ አስደሳች እና ስኩ ቤተሰባዊ ህይወቶች ሲመጡ ያሳያል። የድሀድሀ ገበሬ በረሀብ የሚስቱን ትእግስት ይፈትናል። ሚስት ነገርግን ታጋሸነትን በመስበክ ባሏን ጥቅመ ቁጠባን አጣፍጣ ታስተምራለች። እንደተለመደው በእየለቱ ያለውን ምግብ በመመገብ ለነገ ባዶ ከመሆን ይልቅ፣ ከተለመደው ውጭ ምግቡን እያሻገሩ ተርበው በመቆጠብ እንዲኖሩ ታደርጋለች። መራራ ህይወታቸውን ለመቀየር ሚስት ባሏን በማነሳሳት፣ በቀለብነት ያጎደለችውን ዘር በልመና ከቤቶቿ (የቀድሞ ቤተሰብ) ተበድራ በማግኘት ሐምሌን እንዲያርስ ታደርጋለች። እስከ ጥቅምት ድረስ በጥን ችግር፤ ግን በስረ ማሳው እንደጠነከሩ፤ ጥቅምት ውስጥ በትኩስ እሸቶች ይንበሸበሻሉ። ከብቶቻቸውም አርሰዋልና-ሰብል-እስኪደርስልን-ይሸጡ-ከሚለው ቅድመ-መኸር የአስገዳጅ-መፍትሔነት በሚስት ቁጡ ውሳኔ ተረፉ፨ በህዳር፤ ለድግሱ የእህል ግብአቶችን ተበድረው፣ ደቦ ይጠራሉ። የስረ ማሳቸው ስኬት ዜና ተሰምቶ የበቀለው ታጭዶ ባል በሚትስ ፈቃድ የስራእድል የለመነውን አጋዥ እንዲሆነው ይቀጥራል፤ ለሷም ደንገጡር አርጉኝ ያለችን ይቀጥራሉ። ህይወታቸው በኑሯቸው ተሻሽሎ፣ እዳዎቻቸው ተመልሰው፣ በማህበረሰቡ ተከብረው፣ የካቲት ላይ በደስታ ግብር ከፍለው፣ ወደሚስት ቤቶች ብዙ ስጦታ አስይዘው ከቀጠሯቸው ጋር ለፋሲካ አክፋይ፣ በዚህኛው ጊዜ ብልፅግ አስችሏቸው፣ ይሄዳሉ። ደስተኛ ጊዜ አሳልፈው “ሰው መሆናቸውን” ካሳዩ ወዲያ፣ የተክ